እንዴት መረጃን በአግባቡ እንደምናስተላልፍ | How to Properly Share Information

27972292_196046097652349_260543867024859421_n.jpg

አላስተዋላችሁም እንጂ 95%ቻችሁ (ክርስቲያንም ሆናችሁ ሙስሊም በተለይ በፌስቡክ ላይ) ምን ያህል ሌቦች እንደሆናችሁ ተገንዝባችሁ ትቆጠባላችሁና አንብቡት!!!

https://www.facebook.com/habeshasnetwork/photos/a.1874684612799344.1073741828.1834060100195129/2079551338979336/?type=3&theater

 

እንዴት መረጃን በአግባቡ እንደምናስተላልፍ | How to Properly Share Information

 

በአሁኑ ጊዜ፣ በሶሻል ሚዲያ ላይ፣ በተለይ በሀበሾች የሚተላለፉት መረጃዎች አብዛኛዎቹ ምንጭ አልባ ሆነው ይስተዋላሉ። ይህ ደግሞ አግባብ አይደለም:: ከዚህ በፊት በዮቱብ የለቀኳቸው ቪዲዮዎች ላይ እንደተመለከታችሁት ብዙ ሰዎች ባለማስተዋል፣ ቅንብሮችን ተአምር እያሉ በማሰራጨት እራሳቸው ተሳስተው ብዙዎችንም እያሳቱ ይገኛሉ። የዚህ ሁሉ መንስኤ ታዲያ ምንድነው ካላችሁ፣ አንዱና ዋናው ምክንያት ለምንጭ (source) ያለን አመለካከት በጣም አነስተኛ ስለሆነና የምናሰራጫቸውን ከየት እንዳገኘናቸው ሳንጨምር እንደየራሳችን ነገር አድርገን ስለምናሰራጭ ነው።  ሆን ብለው ቅንብሮችን እንደተዓምር የሚያሰራጩትም ሰዎች፣ ማለትም ጀማሪዎቹ፣ ይህን የአለማስተዋላችንና ለምንጭ የግዴለሽነታችንን ክፍተት አግኝተው በጭንቅላታችን እየተጫወቱብን ይገኛሉ።

ስለዚህ አንድን ነገር በሶሻል ሚዲያ ስናስተላልፍ ወይም ፖስት ስናደርግ ለምናስተላልፋቸው ነገሮች ያገኘንባቸውን ምንጮች ማካተት በጣም ወሳኝ ነው።

በመሆኑም አንድ ሰው ፖስት ያደረገውን ነገር ዝም ብለን ዶውንሎድ እያደረግን ብቻ የራሳችን እንደሆነ አድርገን  ያለምንጭ ከእንደገና መልሰን ያንኑ ፖስት ማድረግ አግባብ አይደለም። አላስተዋልነውም እንጂ ይሄ ራሱን የቻለ ሌብነት ነው። የሚያሳዝነው ደግሞ፣ ለምሳሌ በአንድ ቪድዮም ሆነ ፎቶ ላይ፣ ባለቤቶቹ ፊርማቸውን ወይም ሎጎአቸውን ቢያስቀምጡም እንኳ፣ እነዚህ ሪፖስት የሚያደርጉት ሰዎች የባለቤቱን ፊርማና ሎጎ ቀርፈው አውጥተው ወይም በራሳቸው ሎጎ ሸፍነውት ያለምንም ምንጭ እንደራሳቸው ነገር ፖስት ያደርጋሉ። ይሄ ግን በጣም ነውር ነው። ብዙ ሰዎች ለመታወቅና ተከታይ ለማብዛት ብለው፣ “ይሄንና ይሄን አስትላልፍላቸዋለሁ ፎሎው አድርጉኝ” እያሉ፣ አንዴ የተላለፈውን ነገር ሼር ማድረግ ወይም በአግባቡ ማሰተላለፍ ሲችሉ፣ እነሱ ግን እንደአዲስ የራሳቸውን ሎጎና ፎሎው የሚደረጉበትን የሶሻል ሚዲያ አካውንታቸውን እየጨመሩ ነገር ግን የሚያሰራጩትን ከየት እንደአገኙ ሳይገልፁ የአንዱን ስራ እንደራሳቸው ያሳያሉ። ይሄ ግን ተገቢ አይደለም። ደግሞ እኮ የሚያስተላልፏቸውን ነገሮች በአግባቡ ያገኙባቸውን ምንጮች ቢያካትቱ ላይክ/ሼር ከማግኘትና፣  ፎሎው ከመደረግ የሚያግዳቸው ነገር የለም። ስለዚህ እንደዚህ አይነት ነገሮችን በአግባቡ ቢያደርጉ መልካም ነው።

እስቲ መለስ ብለን እናስበው፣ የፖስቱ ባለቤት እኮ ያንን ለህብረተሰቡ ሲያቀርብ ብዙ መስዋዕትን ከፍሎበት ነው። አንድ ሰው አንድን ነገር ሲያቀርብ ለህብረተሰቡ ጥሩና ጠቃሚ የሚያሰኘው ብዙ ጊዜ፣ ጉልበት፣ እና ገንዘብ ከፍሎበት ነው እንጂ ዝም ብሎ እንዲሁ ሚከናወን ነገር ያለ አይመስለኝም። ፈጣሪ ብቻ ነው በነዚህ ሁሉ ሳይወሰን ቃል ብቻ ተናግሮ ሁሉንም ማከናወን የሚችለው። ጊዜ ወርቅ ነው የሚባለው እኮ ያለምክንያት አይደለም። ስለዚህ ይህን ሁሉ መስዋዕት ከፍሎ ነገሩን ለአዘጋጀው ባለቤት በአግባቡ ክረድት ወይም ዋጋ ልንሰጠው ይገባል።

አንድን ነገር ፖስት ስናደርግ እራሳችን የነገሩ ባለቤት ካልሆንን በስተቀር መካተት ካለባቸው ወሳኝ ነገሮች መካከል ሶስቱ፡- ስም፣ ርዕስ፣ እና የመነሻው ምንጭ ናቸው። እነዚህን ነገሮች አካትተን የአንዱን ሰው ስራ የትም ቦታ ፖስት ብናደርግ ምን ጊዜም ባለቤቱ ማን እንደሆነ በቀላሉ ማውቅ እንችላለን። በሌላም በኩል ብንወስደው፣ ያን ጊዜ ለክፉም ለደጉም፣ ውሸትም ይሁን እውነት፣ ተጠያቂው ባለቤቱ ይሆናል ማለት ነው።

ቆይ፣ ለመሆኑ ለምሳሌ አንድ ሰው አንድን ነገር ለህብረተሰቡ ይጠቅማል ብሎ ጊዜ ፈጅቶበት አዘጋጅቶ ፌስቡክ ላይ ፖስት ሲያደርግ አንዴ ፖስት የተደረገውን ነገር ሌላው ደግሞ ሼር ማድርግ ሲችል ለምን ያንኑ ዳውንሎድ አድርጎ ከእንደገና ፖስት ማድረግ አስፈለገ? እኔ ለምሳሌ የኔ ያልሆኑትን ነገሮች ዝም ብዬ አይደለም አውርጄ በራሴ አካውንት የምለቃቸው።

እስቲ የራሴን እንደምሳሌ አድርጌ በአግባቡ መረጃዎችን እንዴት ማሰራጨት እንዳለብን እንመልከት፦ ይህን ሊንክ ከፍታችሁ ብታዩ ( https://www.facebook.com/habeshasnetwork/videos/2041024909498646/ ) የዶክተር ወዳጄነህን ቃለምልልስ ቪዲዮ ሳስተላልፍ፣ በድስክሪፕሽኑ ላይ ያካተትኳቸው ነገሮች እንደሚከተለው ነው፦
\\\
«ተዋሕዶ ኢየሱስን አታውቅም ማለት በጣም ትልቅ ስሕተት ነው …. ማርያም እናቴ ናት [ስንል እየሱስን ከፍ እናደርገዋለን እንጂ ዝቅ አናደርገውም]»
– ፓስተር ዶ/ር ወዳጄነህ
ከExodus TV Show የተወሰደ
ሙሉውን ቃለ-ምልልስ ለማየት:- https://www.youtube.com/watch?v=qVxsLYKQQ5Q  ///

ያካተኩት እንግዲህ፡
– ርዕስና የእሱን ጥቅስ ከነስሙ (የጥቅሱን ባለቤት ለማሳየት)
– ቪዲዮውን ከየት እንደአገኘሁና ሙሉውን ደግሞ ከዋናው እንድታዩላቸው ልንካቸውን አካተትኩ ማለት ነው።
– ቪዲዮውን ደግሞ እራሱኑ አውርጄ ሳይሆን፣ እኔ እንዲተላለፍ የፈለግኩትን ፓርቶች አውጥቼና አንድ ላይ አድርጌ ለየት ባለ አቀራረብ ነው ያስተላለፍኩት።

ቀደም ብዬ እንዳልኩት፣ ብዙ ነገሮች ያልምንጭ ሲሰራጩ እያየን ነው። ለምሳሌ ከብዙዎቹ አንዱን በአግባብ ያልተሰራጨ ፖስት ላሳያችሁ፡

ለምሳሌ ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ ከፍታችሁ ቢታዩ በርካታ ሰዎች አንዱን ፖስት አንዱ የፖሰተውን እንደራሳቸው ነገር ምንጭ ሳያካትቱ ሲፖስቱ፣ሲያሰራጩ እናያቸዋለን። ይህ ግን በጣም ነውር ነው። ልንኩን ከፍታችሁ እዩ።

ይሄ ብቻ አይደለም፣ የፈለገ ቪዲዮም ይሁን፣ በተለይ ከፊልም የተቀነጨበ ቪዲዮ ከየትኛው ፊልም እንደተቀነጨበ፣ የተሳለ ፎቶም ይሁን ይስዕሉ ባለቤት መታውቅ አለበት፣ ፅሁፍም ቢሆን ፀሃፊው፣ አባባልም፣ ወዘተ ቢሆን ባለቤቱን ማወቅ ያስፈልጋል። መረጃን በአግባቡ ስናሰራጭ ነው ታሪክን ለትውልድ ማስተላለፍ የምንችለው።

በአግባቡ ክረድት ባለመስጠታችን ምክንያት ብዙ ታሪካዊ ነገሮች የሚነገሩት በግምት ሆነው ቀርተዋል። ለምሳሌ አንድ አንድ ታሪኮች ሲነገሩ ብዙ ጊዜ  “እዲህ ነው ትብሎ ይገመታል” ወይም “ይህን ይሰራው እገሌ ነው ትብሎ ይገመታል” የሚባሉ አባባሎች አሉ። አያችሁ አይደል? ይገመታል ነው የሚባሉት በስራዓቱ ስላልተሰራጩና ትክክለኛው መረጃ ስለጠፋ ማለት ነው። በድሮ ጊዜ እንኳን ነገሮች ያን ያህል አመቺ ስለአልንበሩ ሊሆን ይችላል። አሁን ግን ተክኖሎጂው በጣም የረቀቀበት ጊዜ ላይ ነን። ስለዚህ በተቻለን መጠን መረጃዎችን በአግባቡ በማሰራጨት ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ ብዬ ላሳስባቸው እወዳለሁ!

ሃሳቤ ከገባችሁና ከተስማማችሁበት ላይክ፣ ሼርና ኮመንት በማድረግ ብታሳዩኝ ደስ ይለኛል። ይሁላችሁንም ሃስብ ጊዜ እስከፈቀደ ድረስ አነባቸዋለሁ፣ እስካሁንም የሰጣችሁኝን ኮመንቶች እያነበብኳቸውና እየተማርኩባቸው እገኛለሁ። እንማማር ባልኩት መሰረት ጥሩ እየተማማርን ነው ብዬ አስባለሁ። ለምሳሌ ከእናንተ አስተያየት ከተማርኩባቸው ነገሮች አንዱ፣ እኔ በምለቃቸው ቪዲዮዎች የሰውን ማንነት ላለማጋለጥ ፎቶአቸውንና ስማቸውን እየደብቅኩ ቢሆንም ስለአንዱ ተዋቂ ግለሰብ ስናገር ግን፣ አንዴ ተዋቂም ስለሆነና፣ ስለቅንብር አደጋዎች ስናገር በቤተክርስቲያን የሚታወቁትም ሰዎች ጭምር ቅንብርን እንደ እውነት እያስተማሩና እንደምሳሌ እየተጠቀሙት ይገኛሉ ላልኩት እንደማስረጃ ይሆነኝ ዘንድ የግለሰቡን ስምና ፎቶ ሳይቀር ገልጬ ነበር። እናም አንዳንዶቻችሁ ያ ተገቢ እንዳልሆነ በኮመንት ነግራችሁኝ ነበር። እኔም እንደዛ ያርግኩበትን ምክንያት በዚህ መልኩ ምላሽ ሰጥቼ ነበር፡

“እኔም ከመልቀቄ በፊት ስሙ ያስፈልጋል ወይስ ይደበቅ እያልኩ ሳሰላስል ነበር። ግን ያን ለማድረግ የወሰንኩት በዘማሪያንና በሌሎችም ተዋቂ የቤተክርስቲያንአገልጋዮችም ሆነ በዝነኛች ስም አካውንቱ የሚከፍቱ ሰዎች ስላሉ, ይህ ግን እንደዛ እንዳልሆነና በእርግጥ እንደሱ ያሉ የበተክርስቲያን ሰዎችም ጭምር ቅንብርን እንደ እውነት እያወሩና እያሳመኑ ነው ላልኩት እንደማረጋገጫም ይሆን ዘንድ ነበር።

ሲጀመር፣ በኮመንትም ደግሞ ተፅፎለት ነበር, ግን ምንም ያደረገው ለውጥ የለም።

ስለዚህ ሰዎች ወደፊት ከእሱ የሚለቀቁትን እንደዚህ አይነት ነገሮች እንዲመረምሩም ብዬ ነው እሱ ካላስተካከለ ማለት ነው።

ይህም ልክ ካልሆነና ከተሳሳትኩኝም ፈጣሪ ይቅር ይበለኝ, እሱንም ይቅርታ ጠይቄ ቪድዮውን አስተካክለዋለሁ።  ስለሀሳቡ አማሰግናለሁ, ይህም እርስ በእርስ ከምንማማርባቸው መንገዶች አንዱ ነው ብዬ አስባለሁ።”

በማለት ምላሽ ብሰጥም፣ የናንተን አስተያየት በማገናዘብና የዛን ግለሰብ ማንነት ካላሰውቅኩ ፌክ አካውንት ነው ብለው የማያምኑኝ እንደሚኖሩ ሁሉ የሚያምኑኝም ሊኖሩ እንደምችሉ በመገንዘብ ስሙን ማጥፋት የለብኝም ብዬ ያንን ቪዲዮ አስተካክየዋለሁ ማለት ነው። በድጋሚ ስለአስተያየታችሁ ሁሉ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ። ጥሩ እየተማማርን ነው፣ አሁንም እንማማር!

ሁላችንም ብንማማር የት በደረሰን ነበር!!

 

Advertisements

One comment

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s