ማጣሪያ | EthioFactCheck: በታይላንድ አገር የበቀለው “ሚስጥራዊ ዛፍ” እየተባለ ያለው የሴት ቅርፅ ያለበት ፍሬ እውነት ነው?

2fakeposts

womenshapedfruits

ሙሉውን ገለጻ እንዲህ አቅርበውት ነበር፦
 በታይላንድ አገር የበቀለው ሚስጥራዊ ዛፍ እየተባለ ያለው ዕራቆቷን የምትመስል የሴት ቅርፅ ያለበት ፍሬ 
Share~Tag~Like~Comment ይደረግ!
ከታች የምትመለከቱት አክሽን ፊልም ወይም ፎቶ ሾፕ(photo shop) እንዳይ መስላችሁ። ትክክለኛ በታይላድ የበቀለው ተፈጥራዊ ተክክል ነው ። ለማረጋገጥ ያህል ይህ ተጭነው vedio ይሁን ሌላ በgoogle ማየት ይቻላል።
https://www.mirror.co.uk/…/mystery-tree-bears-fruit-shape-8…
https://m.youtube.com/watch?v=L3HCHxCNVu0

የዚህ ዛፍ ሚስጥራዊነት በሳይነሳውያን ፈላስፋዎች እያነጋገረ ይገኛል፡፡ ዛፉ ፍሬ የሚሰጠው እንደሌሎቹ ተክሎች በየ አመቱ አደለም፡፡
የዚህ ተክል ሚስጥራዊነት የሚጀምረው የፍሬ ወቅቱ 20ዓመት መሆኑ ላይ ነው፣ በ20 ኣመት 1 ጊዜ የሚያፈራው ሲሆን ዛፍ ፍሬው ደግሞ የሴት ልጅን ቅርፅ መያዙ ብዙዎችን እያነጋገረ ይገኛል፡፡

ሃይማኖት አላባ በሆነው ሳይነሳዊ ፍልስፍና ሳይሆን ሃይማኖታዊ በሆነ መፅሐፍ ቅዱስ መሠረት አድርገን ከዓለማችን አያይዘን ባለችኝ በጣም ትንሿ ዕውቀቴን ምስጢሩን ላካፍላችሁ ።
እግዚአብሔር አምላካችን አዳምና ሔዋን ወደ ገነት ካስገባቸው በኋላ ለእግዚአብሔር ተገዢዎችን መሆናቸውና ፆም ለማስተማር ከሁሉም ፍሬ ብሉ ከአንዷ ዛፍ ፍሬ(ዕፀ በለስ) ግን እንዳትበሉ፥ ከበላችሁ ግን ትሞታላችሁ ብሎ ትዕዛዝ ሰጣቸው። አዳምና ሄዋን በገነት 7ዓመት ከ3ወርና ከ17 ቀን ከኖሩ በኋላ የዲያብሎስ የሐሰት ምክር ተቀብለው ሁለታቸው ከዛፉ ፍሬ በልቶው የክብራቸው የነበረው ብርሃን ተገፍፎ ዕራቆታቸው ሆኑ፤ የሞት ፍርድም ተፈረደባቸው(ዘፍ 3፥7)።
ታድያ ይቺ በታይላድ ያለችው ምስጥራዊ የዛፍ ፍሬ መፅሓፍ ቅዱስ አልገባ ያለው ትውልድ ትምህርት ይሆን ዘንድ በሚበላ ፍሬ ሔዋን ዕራቆቷን ሁና እንደነበረች ታሳያለች ።
ሌላ በተጨማሪ የዚህ ትውልድ ሃይማኖት መሠረቱ የሆነ ባህላዊ አለባበስ ጥሎ የኢሊሙናቲ የሆነ የምዕራባውያን አለባበስ ፣ ወደ ዝሙትና ግብረ ሰዶም የሚያዳርግ አለባበስ ናፋቂና ተመልካች በመሆኑ በእግዚአብሔር የተፈጠረችው ተአምረኛ ተክል ትምህርት ይሆናቸው ዘንድ ፍሬዋን ልብስ የሌለባት የተራቆተች ሴት መስላ የሚሰማት ካገኘች ከዚህ ሩቁ ሽሹ ትላለች።
በየቡቲኩ የሚገኘው ልብስ የሌለው የሴት ይሁን የወንድ ቅርፅ ያለው አሻንጉሊት ከየት የመጣ ይመስላችኋል? መልሱ ግብረ ሰዶም የሚያስፋፉ ከምዕራባውያ አገሮች ተኮርጇ የመጣ ነው ። በታይላድ ያለችው ግን ህፍረቷን በእጇ ሸፍና ልባችን አላስተውል ሲል ሂወት ካለት ዛፍ ወጥታ ዕራቆታችሁ አትሁኑ ትላለች። የእግዚአብሔር ስራ ግን ድንቅ ነው!

ዓለም በዛፏ ብንመስላት የዛፏ ፍሬ ደግሞ ሴት እህቶቻችን (ዕራቆታችሁ ለምትሄዱ ሴቶች ነው የሚመለከተው) ብንመስለው ውጤቱ ይህ ነው።
የወንዶችም የተቀደደ ሱሪ የለበሰ፣ ሱሪውን ከቂጡ በታች ዝቅ ያደረገ፣ ፀጉሩን ያሳደገ ፣ የእግሩን ጫማ አጋፋ የሚመስል የምታሳይ የዛፍ ፍሬ ካለም ወዲህ በሉን። 
ተጨማሪ ሐሰብ ካላችሁ ጨሙሩበት። በስጋዊ ፍልስፍና የሚሠጥ ሐሳብ ግን ተቀባይነት የለውም።”

እውነታው፡ የሰው ሰራሽ ቅርጽ ነው!


በአጭሩ እንደዚህ አይነት የፍራፍሬ ቅጾች እንዴት እንደሚሰሩ ከዚህ በታች ያለውን ቪድዮ አይቶ መረዳት ይቻላል።

👉🏽 “ሳይገሉ ጎፈሬ ሳያስረግጡ ወሬ” ነውና፣ ለወደፊቱም አሉባልታዎችን በዚህ በETHIOFACTCHECK | ማጣሪያ ላይ ያጣሩ (ያረጋግጡ) ወይም ይጠይቁ!

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s