About

ሰላም ጤና ይስጥልኝ ውድ ወገኖቼ!

እኔ ዩሔ እባላለሁ፣ በያላችሁበት ሰላምታዬ ይድረሳችሁ።

ይህ የሚታዩት “Habesha Social Network – እንማማር” የተሰኘ፣ ለኛው ሀበሾች የተዘጋጀ ብዙ ነገሮችን የምንማማርበት የFacebook Page ነው። ገፁ ላይ በየጊዜው አዳዲስና ጠቃሚ የሆኑ፣ ትምህርታዊ ነገሮችን በቪዲዮም ሆነ በጽሁፍ መልክ በገፁ ላይ አስተላልፋለሁ፣ የሚተላለፉትንም ነገሮች ጠቃሚ ሆኖ እንደምታገኟቸው ተስፋ አደርጋለሁ። የፔጁን ሊንክ ከታች Descriptionኑ ላይ አስቀምጬላችኃለሁ፣ ገብታችሁ ፔጁን Like በማድረግ Post የማደርጋቸውን ነገሮች መከታተል ትችላላችሁ። ያው ደግሞ ያወቁትን ለሌሎችም ማሳወቅ መልካም ነውና፣ እናንተም የFacebook ገፁን Like በማድረግና ለሌሎችም Share በማድርግ እርስ በእርስ እንማማር!

ወገኖቼ ፣ በጥብቅ ላሳስብ የምፍለገው ነገር ደግሞ፣ እባካችሁ በየትም ቦታ ቢሆን ስንወያይም ሆነ ኮመንት ስንደራረግ፣ በመሰዳደብና በመናናቅ አይሁን! ፍቅር፣ መከባበርና፣ መተሳሰብ ይኑረን።

ለምሳሌ፣ እኔን አንድ ሰው ዝም ብሎ ቢሰድበኝ፣ አዝንለታለሁ እንጂ መልሼ አልሳደብም፣ አልፈርድበትምም። ምክንያቱም ያ ሰው ከአስተዳደጉ ወይም በሕይወቱ ካሳለፋቸው ነገሮች የተነሳ በስድብ ባህሪይ የተጠቃ ወይም ተጎድቶ ነው እንጂ ወዶ አይመስለኝም።

ሰዎች ነንና ሁላችንም ተሳስተን ልንታረም እንችላለን። ስለዚህ በትህትና፣ “የኔ ወንድም/የኔ እህት፣ ይሄ ልክ አይመስለኝም። ነገሩ እንዲህ ቢሆን የተሻለ ነው ብዬ አስባለሁ፣ እንደዚህ ቢሆን ጥሩ ነው” እና ወዘተ በማለት ሃሳባችንን በማቅረብና ጉዳዩን በእርጋታና በትህትና አንዱ ሌላውን ቢያስረዳ የት በደረስን!?!? እያንዳንዳችን ስንለወጥ ነው ሀገሪቷ፣ ብሎም ዓለም ልትለወጥ የምትችለው!

ጋዜጠኛ ግሩም እንዳለው፣ «ትልቅ ነበርን፣ ትልቅም እንሆናለን!»

ትልቅ የምንሆነው ታዲያ፣ እርስ በእርስ ስንማማር ነው። እርስ በእርስ የምንማማረው ደግሞ የምናውቀውን ለሌሎቻችም በማካፈል ወይም ሼር ስንደራረግ ነውና፣ ሼር እያደረግን እርስ በእርስ ስንማማር! ኮመንት አድርጉ፣ እኔም ከናንተ አስተያየት ብዙ ነገር እማራለሁ። ስለዚህ ሁላችንም አብረን እንማማራለን ማለት ነው።

Advertisements